Friday, March 15, 2013

የፍቅር ስፌት ትችይ ይሆን?

ፍቅሬ ሆይ
የፍቅር ስፌት ትችይ ይሆን?
ማንቃት ግራምጣውን
ባለላ አስጊጦ?
መሰበዝ ሰበዙን?
ወንድ ነኝ እና ውጥኑን ልወጥን
ከቻልሽ መቋጨቱን
ማሳመር ስፌቱን፤
ግራምጣ አንቅቶ
አለላ አልሎ.....
አክርማውን ነቅለሽ ሰበዙን ከሰበዝሽ
ፍቅር መስፋት ከቻልሽ፤ በወስፌ እዬወጋሽ
ግድ የለሽም ለውጥኑ
በወንድነት እኔው ልወጥን
መቀልበሱን ግን አደራ ላንች
በሴትነት ውጥኑን መቋጨቱን።

Z.K. /March 15, 2013

No comments:

Post a Comment